Tuesday, March 25, 2014

አዲስ አበባ በጩኸት ልትናጋ ነው። ቀኑ ዛሬ ተወስኗል፣ መጋቢት 28/2006

የአዲስ አበባው ‹‹የእሪታ ቀን›› ተቆረጠ

(በነብዩ ሃይሉ) የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል የፓርቲውን ደብዳቤ ተቀብሏል::
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ መሰረታዊ ችግሮች እየተባባሱ ከመምጣት ውጪ ለውጥ ማሳየት ባለመቻላቸው ለዚህ ተጠያቂ መሆን ያለበትን የከተማይቱን አስተዳደርና ገዢውን ፓርቲ የሚቃወም ‹‹የእሪታ ቀን›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 28/2006 (April 4, 3014) ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደርግ አስታውቋል፡፡
በዛሬው እለት የፓርቲው ተወካዩች ለአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል ስለ ሰልፉ የሚገልጽ ደብዳቤ በማስገባት ተመልሰዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ቀነ ገደብ የፓርቲው ጽ/ቤት ከሚገኝበት ቀበና በመነሳት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ አንድነት ህዝብ ግኑኝነት አቶ ያሬድ አማረ አስታውቀዋል፡፡
udj erita ken press release
Source: Fenote Netsanet

No comments:

Post a Comment