Wednesday, March 26, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ሉቀመንበር በአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ስኬታማ ወጣት መሪ ተብለው ተመረጡ። በራስ ፓርቲ እና ጭፍን ደጋፊ ታላቅ መሪ ከመባል በገለልተኛ ሃገር ያውም በአሜሪካ ስኬታማ መሪ መባል ምንኛ ደስ ይላል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሉቀመንበር በአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ
ስኬታማ ወጣት መሪ ተብሇው ተመረጡ


አዲስ አበባ፡- የሰማያዊ ፓርቲ ሉቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ
ስኬታማና በቀጣይነትም ሀገራቸውን መምራት የሚችለ ወጣት መሪ ተብሇው ተመረጡ፡፡

ከፓርቲው የህዝብ ግንኙነት የተገኘው መረጃ እንደሚያመሇክተው ኢንጅነር ይልቃል ሇአሸናፊነት የበቁት ‹‹የአሁኑ
ወጣት የአፍሪካ መሪና ወደፊትም ሇአገራቸው መሪ ሉሆኑ የሚችለ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ስራ የሰሩ መሪዎች
መካከል በተደረገ ውድድር በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት›› መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው፡፡

ሉቀመንበሩ ሇአሸናፊነት መብቃታቸው ይፋ ከመሆኑ በፊት የአሜሪካ መንግስት የኢንጅነር ይልቃልን መሰረታዊ
የሚባለትን የፖሇቲካ ቆይታ፣ የትምህርት ዝግጅት፣ በፖሇቲካው ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ እና የመሳሰለትን
መረጃዎች ወስዶ እንደነበር ሇማወቅ ተችሏል፡፡

ኢንጅነር ይልቃል በዚህ ውድድር በመመዘኛዎች መሰረት በማሸነፋቸው በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት
የጉብኝት ግብዣ ተደርጎሊቸዋል፡፡ በመሆኑም የአሜሪካ መንግስት ሙለውን ወጭ ሸፍኖ ሇሶስት ሳምንት በአሜሪካ
የመንግስት አወቃቀርና ዴሞክራሲን ጨምሮ በተግባር የሚሰጡ ስልጠናዎችን የማግኘትና የአሜሪካ መንግስት
ባሇስልጣናትም ባለበት ከተሇያዩ ተቋማት ጋርም ሇመገናኘት እድል እንደሚኖራቸው ያገኘነው መረጃ ያመሇክታል፡፡

‹‹የሉቀመንበሩ ሇዚህ ሽልማት መብቃት አዲሱን ትውልድ ወደ ፖሇቲካው ሇማምጣት በሚያደርገው ጥረት እንደ አንድ
ማበረታቻ ተደርጎ ሉወሰድ እንደሚችልና ሰማያዊ ፓርቲ እያደረገው ሊሇው ሰሊማዊ ትግል ትልቅ እውቅና እንደሆነ
ያሳያል›› በማሇት የህዝብ ግንኙነቱ ያደረሰን መረጃ ይጠቅሳል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ዛሬ ወደ አሜሪካ
እንደሚያመሩም መረጃው ጨምሮ ገልጾዋል፡፡

No comments:

Post a Comment