EthioFreedom
Thursday, July 3, 2014
Sunday, June 29, 2014
Thursday, June 26, 2014
Tuesday, June 24, 2014
ምኒልክ እና አርሲ በወርቁ ፈረደ " ... አንዳንድ ምሁራን ከዚህ አልፈው ጦርነቱ በወራሪው አማራና በሰላማዊው ኦሮሞ መካከል እንደተካሄደው አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው አሳዛኝ ነው፡፡"
ምኒልክ እና አርሲ
ወርቁ ፈረደ
ኢትዮጵያዊው ቢስማርክ ዳግማዊ ምኒልክ፣ አገር ለማስገበር ካደረጓቸው ዘመቻዎች ውስጥ ትልቅ ምከታ የገጠማቸው አርሲ ላይ ነው፡፡ ምኒልክ በአርሲዎች ክንድ ተከታታይ ሽንፈት ከቀመሱ በኋላ፣ በራስ ወልደ ገብርኤልና በራስ ዳርጌ እልክ አስጨራሽ ዘመቻ አማካኝነት፣ አሸንፈው አርሲን ወደ ግዛታቸው ቀላቀሉት፡: በጦርነቱ ከአስገባሪውና ከገባሪው ወገን አያሌ ወታደሮች አልቀዋል፡፡ ውጊያው የተካሄደው፣ነፍጥ በታጠቁ የንጉሱ ወታደሮችና ከጦርና ጋሻ ፈረስ ውጭ ምንም በሌላቸው የአርሲ ጎበዞች መካከል በመሆኑ፣ ከተከላካዩ ወገን ያለቀው በቁጥር እንደሚልቅ እሙን ነው፡፡ የአርሲ ጦርነት ከተካሄደ ከጥቂት አመታት በኋላ፣ ወደ ኦሮሞ ምድር የደረሰው ደ ሳልቪያክ የተባለ የፈረንሳይ ሀዋርያ ከአርሲዎች በሰበሰበው መረጃ ተመስርቶ እንደጻፈው፣ ራስ ደገብርኤል የአርሲዎችን አይበገሬነት ለመስበር ባንድ ቀን ብቻ የአራት መቶ አንጋፋዎችን ክንድ አስቆርጠዋል፡፡ይህ ጻሀፊ፣ ክንዳቸውን ካጡት ትልልቅ ሰዎች ጥቂቶቹን ባይኔ በብረቱ አይቻለሁ ብሏል፡፡
ይህ የታሪክ ዘገባ በዘመናችን ፖለቲከኞች ሁለት ዓይነት ምላሽ እየተሰጠው ነው፡፡ የመጀመሪያው ምላሽ ክስተቱን ‹‹አይደረግም›› ብሎ መካድ ሲሆን፤ በተቃራኒ ወገን ያለው ደግሞ በማጋነንና በማራገብ ተጠምዷል፡፡ባለፈው ሳምንት ሀብታሙ አያሌው የተባለ ጸሀፊ በዚህች መጽሔት ላይ ሲጽፍ፣ የአርሲን የበደል ታሪክ፣ የቡርቃ ዝምታ ልቦለድ ውጤት እንደሆነ ሊያሳምነን ይፈልጋል፡፡ በኔ አስተያየት ይሄ አይነቱ ድርቅና ማንንም አይጠቅምም፡፡ አርሲ በስጦታ ወይም በስምምነት የተደባለቀ አገር አይደለም፡፡ የተገኘው በብዙ አገሮች እንደተደረገው፣ በጉልበትና በነውጥ ነው፡፡በወቅቱ ሰብአዊ ጥሰቶች በገባሪው ወገን ላይ መድረሳቸውን መካድ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሌላው ‹‹እፍኝ ቆሎ ይዞ ወደ አሻሮ›› የሚጠጋው የብሄርተኛው ወገን ነው፡፡ ይህ ወገን፣ የእምቢተኛ ወታደር እጅ ተቆረጠ ሲባል፤ ‹‹ሰላማዊ ሴቶች በሰልፍ እንዲያልፉ ተደርጎ ጡታቸው ተቆረጠ፣ አባዱላዎች ተመርጠው እንዲኮላሹ ተደረገ፡፡ ሚኒልክ ነፍጥ አልበቃ ብሏቸው፣ ፈንጣጣ ፈብርከው ህዝባችንን ፈጁ››እያለ በተደረገው ላይ ያልተደረገ የምናብ ፍሬ እየጨመረ የሚተርት ነው፡፡በተለይ አንዳንድ ምሁራን ከዚህ አልፈው ጦርነቱ በወራሪው አማራና በሰላማዊው ኦሮሞ መካከል እንደተካሄደው አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው አሳዛኝ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱን ፕሮፖጋንዳ ውጤት፣ ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እያየነው ነው፡፡
በሌላ በኩል በጉልበት ሌላውን ማስገበር አያሌ ህዝቦች በፈረቃ ያደረጉት ሆኖ ሳለ፣ አንድ ንጉስና አንድ ብሄረሰብ ብቻ በሞኖፖል የያዘው አድርገው ለማሳየት የሚሞክሩ አሉ፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ጠማማ አስተሳሰቦች ማቃናት ነው፡፡
እስቲ ምኒልክን በጭራቆች ወይም በመላእክት ቦታ ለመመደብ ከመቸኮላችን በፊት፣ ከምኒልክ በፊት ገባር ህዝቦች ምን አይነት ያኗኗር ዘይቤ ይከተሉ እንደነበር እንመልከት፤ ከአርሲ እንጀምር፡፡

Saturday, June 21, 2014
ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት? " ... የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል ሰሞኑን ባወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን ገለጸ፡፡"
ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት?

በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ልማት ትምህርት ክፍል ሥር የኢኮኖሚ ጥናት የሚያካሂደው የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል (The Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI)) ሰሞኑን ባወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን ገለጸ፡፡ የጥናቱ ዘገባ ኢህአዴግ በየጊዜው ከሚያቀርበው የዕድገት ስሌት ጋር በግልጽ የሚጋጭ መሆኑ ተነገረ፡፡
በዓለማችን በሚገኙ 108 በማደግ ላይ ባሉ አገራት በየጊዜው ጥናት የሚያካሂደው ማዕከል ጥናቱን በሚያካሂድበት ጊዜ 10 መለኪያዎችን እንደ ግብዓት እንደሚጠቀም ይናገራል፡፡ እነዚህም በሦስት ዘርፎች የተጠቃለሉ ናቸው – ትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ፡፡ በተለይ በኑሮ ሁኔታ ሥር ኤሌክትሪክ፣ ጽዳት፣ የሚጠጣ ውሃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ወዘተ በግብዓትነት ተወስደዋል፡፡
በዚህ ዓይነት እኤአ ከ2002 እስከ 2011 ድረስ ያለውን መረጃ በማጠናቀር በወጣው ዘገባ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ100 ሰዎች መካከል 87ቱ ድሃ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን 58ቱ ሰዎች ግን መናጢ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ድህነቱ በገጠር እጅግ የከፋ እንደሆነ በመጠቆም ከ100 ሰዎች ውስጥ 96ቱ ደሃዎች እንደሆኑ፤ በከተሞች አካባቢ ግን ከ100 ሰዎች መካከል 46ቱ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአጠቃላይ የአገሪቷ ክፍሎች ከ100 ሰዎች መካከል 31ዱ በቀን ከ20ብር በታች በሚገኝ ገቢ እንደሚኖሩ ጠቁሟል፡፡
Friday, June 20, 2014
ለመለስ ፋውንዴሽን ማሰሪያ እየተባለ በግዴታ የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈልገው በእጅጉ እንደሚልቅ ታወቀ

Jun 20th, 2014 · 0 Comment
Share the joy
ኢሳት ዜና :-

በኦሮምያ ደግሞ ከ205 በላይ ወረዳዎች ሲኖሩ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል። በትግራይ ከ38 ወራዳዎች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ፣ በደቡብ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ሲዋጣ፣ በአዲስ አበባ የሚወጣው ደግሞ እስከ 2 ቢሊዮን ብር ይደርሳል። በመላ አገሪቱ በሚገኙ ወረዳዎች ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣ ሲሆን፣ ለፋውንዴሽኑ ከተበጀተው 300 ሚሊዮን ብር ውጭ ያለው ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅና ቁጥጥር የሚያደርግ አካል አለመኖሩንም ምንጮች ገልጸዋል።
ደሃውበምግብውድነት: ነጋዴውበግብር አርሶአደሩ በማዳበሪያ እዳ እየተሰቃዩ ባለበት ጊዜ ይህን መክፈል አይቻልም በማለት ተቃውሞ ያስነሱ ሰዎች፣ ተቃውሞቸአውን የሚሰማቸው አካል አላገኙም። አንዳንድ ዜጎች ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ለኢሳት በመላክ፣ ዝርፊያው እንዲቆም ህዝቡ ተቃውሞ እንዲያሰማ እየጠየቁ ነው። የመለስ ፋውንዴሽን፣ የቀድሞውን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን የሚዘክሩ ስራዎችን የመስራት አላማ አለው። ፋውንዴሽኑ በህዝብ ፈቃድ እና ከመንግስት በሚሰጥ ገንዘብ ይሰራል ተብሎ ቢነገረም፣ ህዝቡ ለማዋጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ በግዴታ እንዲያዋጣ እየተደረገ ነው። ከህዝብ ፈቃድ ውጭ የተሰራ ፋውንዴሽን ፣ ኢህአዴግ እስካለ ጊዜ ብቻ እንደሚቆይ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፣ ፋወንዴሸኑ ከደሃው ኢትዮጵያዊ ገንዘብ መሰብሰቢያና ሃብት ማካበቻ መሆኑንም አክለዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)