የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፒቴን አስመራ ላይ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀለ፤ * መንግስት አላስተባበለም
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ አየር ሃይል አባላት ገዢውን የኢሕአዴግን መንግስት በመክዳት ወደ ተለያዩ ሃገራት የሚያደርጉትን ስደትቀጥለዋል። የኤርትራ ሚዲያዎች የመንግስታቸውን ቃል አቀባይ በመጥቀስ እንዳስነበቡት ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሚግ 23 አብራሪ የሆነው ካፒቴን ዳንኤል የሽዋስ ስርዓቱን ጥሎ አስመራ ገብቷል።እንደኤርትራ ሚዲያዎች ገለጻ ከሆነ ካፒቴን ዳንኤል የሺዋስ ኤርትራ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ተቀላቅለዋል።
ሚዲያዎቹ በምን መልኩ ወደ አስመራ እንደገባ የገለጹት ነገር ባይኖርም ማዕዶት የተባለው የኤርትራውያን የመረጃ መረብየኤርትራን መንግስት ቃል አቀባይ በመጥቀስ ካፒቴኑ ለኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት እጁን የሰጠው ከነ አውሮፕላኑ ነው ሲልዘግቧል።
የኢሕአዴግ መንግስት በመከላከያ ውስጥ ያለውን የዘር አድልዎና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትበቸልታ መመልከት እያንገፈገፋቸው የሚገኙ የሠራዊቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት እየሸሹ ወደ ኤርትራ በመግባት ተቃዋሚዎች
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፒቴን አስመራ ላይ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀለ፤ * መንግስት አላስተባበለም
2/2 እንደሚቀላቀሉ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግስት ካፒቴን ዳንኤል የሽዋስን መክዳት አስመልክቶ ምንም ያወጣው መግለጫ የለም። ዘ-ሐበሻ ከመንግስት አካባቢ ዜናውን ለማረጋገጥ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፒቴን አስመራ ላይ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀለ፤ * መንግስት አላስተባበለም
2/2 እንደሚቀላቀሉ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግስት ካፒቴን ዳንኤል የሽዋስን መክዳት አስመልክቶ ምንም ያወጣው መግለጫ የለም። ዘ-ሐበሻ ከመንግስት አካባቢ ዜናውን ለማረጋገጥ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment