ኦስትሪያዊው የፊልም ተዋናይ እና በኢትዮጵያ የምግባረ ሰናይ ስራዎችን በመስራት የሚታወቀው ‘ሰዎች ለሰዎች’ (Menschen für Menschen) ድርጅት መስራች የሆኑት ካርልሀይንስ ቦም አረፉ።
ህይወታቸው ያለፈው በ86 አመታቸው በትናትናው እለት፣ ሀሙስ በሳልዝቡር ከተማ ነበር። ቦም ለረጅም ጊዜ በህመም ላይ ቆይተዋል። ቦም ኢትዮጵያን ለመርዳት ያቋቋሙት ‘ሰዎች ለሰዎች’ (Menschen für Menschen) የእርዳታ ድርጅት ከተወሰኑ አመታት ጀምሮ በኢትዮጵያዊቷ ባለቤታቸው አልማዝ ቦም ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ወ/ሮ አልማዝ ባሳለፍነው ታህሳስ፣ ባለቤታቸውን ለማስታመም የስራ አስኪያጅነት ስራቸውን አሳልፈው ሰጥተው ነበር።
No comments:
Post a Comment