የቴዲ አፍሮ የዲሲ ኮንሰር መሰረዝ አነጋጋሪ ሆነ ፣ጉዳዩ ከ ኤም
ፕሮዳክሽን ጋር በተያያዘ ነው የሚል እሳቤ አለ !
By maleda times / May 20, 2014 / No Comments
ለሚሞርያል ሳምንት ይከናወናል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት መሰረዙን ከፕሮሞተሮች እና የቴዲ አፍሮ ማናጀር የሆነው ዘካርያስ ጌታቸው በቴዲ አፍሮ ስም በከፈተው የፌስ ቡክ ፔጅ መግለጹ ይታወቃል ይህንንም ተከትሎ በቴዲ አፍሮ ጉዳይ ላይ ተደራራቢ የሆኑ ክሶች ከተለያዩ ቦታዎች ካለፈው አመት ጀምሮ በተከታታይ አቤቱታዎች ሲቀርቡበት ቆይቷል ።እንደ አብነትም ከኬኤም ኤፍ ፕሮዳክሽን እና ፕሮሞሽን ጋር ባደረገው ውል መሰረት የ30.000 የአሜሪካን ዶላር ክስ ሊቀርበበት እንደቻለ እና የማይከፍል ከሆነ ወደ ክስ ሊያመራ እንደሚችል የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ከፕሮሞሽኑ ማናጀር መረጃውን በመቀበል ማቅረባችን የሚታወስ ነው ።
አሁንም ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ ውስጥ አዋቂ ምንጮች የተሰኘው የሬዲዮ ፕሮግራም የቴዲን አዲስ ክስ አስመልቶ በዜና መልክ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን የክስ ጉዳይ ለቴዲ አፍሮ ፣ለቀድሞው ማናጀር አዲስ ገሰሰ እና ለአሁኑ ማናጀር ዘካርያስ ጌታቸው ከዳላስ የህግ ባለሙያዎች አስቸኳይ ምላሽ ሊሰጥበት የሚገባ ብለው ምላሹን እስከ ሜይ 17/2014 ድረስ እንዲመለስ ካልተመለሰ ግን ክሱን ቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት ሊያመራ እንደሚችል አያይዘው የህግ ባለሙያዋ በየግል ኢሜሎቻቸው መላካቸውን ከአንዳንድ ውስጥ አዋቂ ምንጮች የሰማነው ሪፖርት ሲያመለክት እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አይነት መልስ ያልቀረበ ሲሆን ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱ የማያጠያይቅ ነው ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዋሽንግተን ዲሲውን ኮንሰር በመሰረዝ ወደ ኤም M (ሚኪ ዳላስ)ፕሮዳክሽን ወዳለበት ቦታ ላይ የአዲሱን ኮንሰርት ስራ ለመስራት መዘጋጀትበህብረተሰቡ ዘንድ አነጋጋሪ ከመሆኑም የተነሳ ፣ምን ሊያደርግ ነው የሚለው ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ሲሉ ብዙዎች ይገልጻሉ ። ከእነዚህም መካከል ቴዲ ወደ ዳላስ የሚመጣው የተከፈተበትን ክስ ለመከላከል ነው ፣ወይስ ከሚኪ ዳላስ ጋር ያለውን የሙዚቃ ስራ ውል በሰላም ለመጨረስ አለበለዚያ የክሱን ሁኔታ ለማብራራት ያስችለው ዘንድ ጠበቃ ለመፈለግ የሚሉ የተለያዩ ግራ የሚያጋቡ ሃሣቦች ቀርበዋል ፤ይህ በእንዲህ እንዳለ ቴዲ አፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ ባለፈው ረቡእ እለት ወደ አሜሪካ ጉዞውን ለማድረግ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ የነበረ ቢሆንም ከሃገር ቤት ባልታወቀ ሁኔታ የጉዞውንም ጉዳይ ማራዘሙ በጣም ግራ መጋባቱን ውስጣዊ ምንጮቻችን ጠቁመዋል ። የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ከዘሃበሻ ጋር በመተባበር የተሰራ የዜና ጥንቅር።
የቴዲ አፍሮ ማናጀር ዘካርያስ ጌታቸው በፌስ ቡክ የለቀቀው አጭር ዘገባ ይህንን ይመስላል ።ከስር ይመልከቱ፣ሚኪ ዳላስን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ያለውን ሁኔታ አስመልክተን ከሚኪ ፕሮዳክሽን ጋር የምናደርገውን ቆይታ በጥረትእንዲሳካ ለማድረግ እንጥራለን ማለዳ ታይምስ Teddy Afro tps://www.facebook.com/TeddyAfroMusic?hc_location=timeline)
5 hours ago (https://www.facebook.com/photo.php?fbid=414039685402348&set=a.149747718498214.33654.127529064053413&type=1)
Due to unforeseen circumstances, we regret to inform you that, the upcoming concert of Teddy Afro in Washington,
D.C. on Sunday May 25th 2014 will be postponed to a later date. The concert will be rescheduled and the new date
will be announced as soon as possible. We apologize for any inconvenience. All other concerts in the US will proceed.
No comments:
Post a Comment