የእሪታው ጥሪ… በአርበኞች ቀን ይከበራል። (የጥሪ ወረቀቱን ይዘናል)
(EMF) መጋቢት 28 ቀን፤ የኢትዮጵያ አርበኞች የጣልያን ወራሪዎችን ድል አድርገው አዲስ አበባ የገቡበት እና የጣልያንን ባንዲራ አውርደው የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የሰቀሉበት ቀን ነው። ይህ እለት፤ “የድል ቀን” ተብሎ ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ ሲከበር ቆይቷል። እርግጥ አሁን ቀኑ ተቀይሮ የኢትዮጵያ የድል ቀን የሚከበረው ሚያዝያ 27 ሆኗል። ይህም ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ አዲስ አበባ የገቡበት ቀን መሆኑ ነው። (የቀኑ ጉዳይ ብዙ አያከራክርም) አሁን አንድነት ፓርቲ የጠራው የ እሪታ ቀን ከቀድሞው የአርበኞች ድል ቀን ጋር መጋጠሙ ግን ድርብ መልእክት ያስተላልፋል፤ የሚል እምነት አለ።

የአንድነት ፓርቲ ጥሪውን ለማድረግ የተገደደው በተለይ በአዲስ አበባ የሚከሰተውን የውሃ፣ የስልክ እና የመብራት መቆራረጥ በመቃወም ነው። ህዝቡ “ከዛሬ ነገ ይሻሻላል።” በሚል ተስፋ ብዙ አመት በትግስት ጠብቋል። ሆኖም ተስፋው እየተሟጠጠ እንጂ እየተሻሻለ የመጣ ነገር የለም። በተደጋጋሚ በነዚህ መስሪያ ቤቶች ላይ ህዝቡ ቅሬታውን ቢያሰማም፤ ባለስልጣናቱ “የዝሆን ጆሮ ይስጠን” በሚል አይነት ዝምታን መርጠዋል። ተበዳዮች በተናጠል ወደ መብራት ሃይል እና ሌሎች መስሪያ ቤቶች እየሄዱ የሚያሰሙትም እሮሮ የሚደመጥ አልሆነም። እንዲያውም እንደሽሮ ሜዳ ያሉ አካባቢዎች፤ ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ፈቃድ እና ጥያቄ ሳያቀርብ ወደመስሪያ ቤቶቹ በመሄድ የተቃውሞ ድምጹን አሰምቷል።

እንደ አንድነት ፓርቲ መግለጫ ከሆነ፤ “ኢህአዴግ አገር መምራት እንደማይችል አዲስ አበባ ማሳያ ነች” ብሏል። በአሁኑ ወቅት የጥሪው ወረቀት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች እየተበተነ ነው። መጋቢት 28 ቀንም የተጠራው የእሪታ ጩኸት ከዳር እስከዳር ያስተጋባል። ከ73 አመታት በፊት መጋቢት 28 ቀን በአዲስ አበባ የተከበረውን የአርበኞች የድል ቀንም በዚሁ አጋጣሚ ታስቦ ይውላል።
No comments:
Post a Comment