Sunday, April 27, 2014

የህዋሃት መሪዎች ፋሽስታዊ ተፈጥሮ ሲጋለጥ

የህዋሃት መሪዎች ፋሽስታዊ ተፈጥሮ ሲጋለጥ
(አስገደ ገ/ስላሴ፣ መቐለ)

 ህ.ወ.ሃ.ቶ.ች በ 1983 ዓ/ም ስልጣን እንደያዙ ልክ ፋሽስታዊ ደርግ ‘ኢትዮጵያ ትቅደም ያለ ምንም ደም ብሎ!’ የኢትዮጵያ ህዝብ ልብን ለመግዛት እንደሞከረ ሁሉ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችም ስልጣን ከያዙ በኋላ የተቆጣጠሩት መገናኛ ብዙሃን የደርግን ክፋት በመለፈፍ እንዲጠመዱ፣ ባንጻሩ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ጀግነትና መልካምነት አጋነው እንዲዶሰክሩ ተደርገው ነበር።

ሁሉም አይነት ሰብአዊ መብቶች የህግ የበላይነትን እናረጋግጣለን ብዙሃን ፓርቲ ነፃ ሆነዉ እንዲቀሳቀሱ ነፃ ምርጫ በማድረግ በሰላማዊ መንገድ የስልጥን ሽግግር እናደርጋለን በማለት ለጊዜዉ ሁሉም ፓርቲዎች የሚሳተፉበት የሽግግር መንግስት አብዛኞቹ ራሱ የጠፈጠፋቸዉ ፓርቲ በማሳተፍ ሽግግር መንግስት መሰረተ ቆየት ብሎም ህገ-መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን አቋቋመ ህግ-መንግስቱ አቶ ክፍለ ወዳጆ ብዙ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ተፅእኖ በተቻላቸዉ በመከላከል ደሀና ሊባል የሚችል በወረቀት ደረጃ ተዘጋጀ ህገ-መነገስት በዋናነት ያተኩርበት የነበረ በተለይ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በተለይ ደግሞ መለስና ጓዶቹ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት የሚደፍርና ባሀር የሌላት በመሬት የተዘጋች አገር ለመመስረት ጠንክረዉ ይታገሉ ነበር። በዛን ወቅት እንደነ ኢ.ህ.አ.ፓ የመሳሰሉ አንጋፋ ፓርቲ ደርግን ለመጣል አነስተኛ የማይባል አስተዋፅኦ የነበራቸው ለማግለል ዋና ጥረት ነበር ኦ.ነ.ግ.ም ከሽግግሩ መንግስት እንዲወጣ ተደረገ። በቃ በኢትዮጵያ የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች የነበረ ጉራና ውሸት ሳይጎረምስ አረጀና ገና በጥዋቱ የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች አስተሳሰብ ያልተቀበለ ሁሉ ጥይት አጉርሰዉ ማለት ጀመረ ኢ.ህ.አ.ፓ ኦ.ነ.ግ ተመቱ ሌሎች አነስተኛ ፓርቲዎች ወደ ስልጣን ያወጡዋቸዉ የህ.ወ.ሃ.ት ታጋዮችም ከ 32000 ታጋዮች በላይ አሰሩዋቸዉ ደብዛቸዉ አጠፍዋቸዉ ኣበረርዋቸዉ በትግራይ ክልል ከተማና ገጠር ነዋሪዎች ህዝብም ስለ ኤርትራ ሪፈረንደም ስለ የባሀር በር ስለ ዲሞክራሲያዊና ሰብኣዊ መብት ስለምልካም አስተዳደር ጥያቄ ያነሱ ወገኖች ታሰሩ ከቀላል እስከ ከባድ ቅጣት ተቀጡ ነፃ ፕሬስ ተዘጉ ወይ እንደ ጠላቶች ታዩ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ በማድረግ ዲሞክራስያዊ ህዝባዊ መንግስት እንመሰርታለን የሚል ጉራና ውሸት ህልም ሆኖ ቀረ። ነፃ የተቀዋሚ ፓርቲ እንቅስቃሴ በድህንነት እጅ ገባ። የህግ የበላይነት ለህዝብ መሆኑ ቀርቶ በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች እጅ ወድቆ እስከ አሁኑም አቃቤ ህግ ድህንነት ሁሉ ለህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ጠባቂና ህዝብን ማፈን ዋና ስራቸው ሆኖም ይገኛል፣ ዳኞችም ነፃነታቸው የተጠበቀ አይደለም የህግ ጠበቃዎም በህ.ወ.ሃ.ት አመራር አይን በጠላትነት ተፈርጀው የዳኝነትን ውሳኔዎች እንደ አፍራሽ ጠላት ሆነው ተፈርጀዋል።

 በአጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች መምህር፣ሃኪም፣ተማሪ፣ የዩንቬርስቲ ህ/ሰብ ከህ.ወ.ሃ.ት አመራር ውጭ የሚያስቡ የህ.ወ.ሃ.ት
ፓርቲ አባል ያልሆኑ በጠላትነት ይታያሉ።ትምህርት ቤት ከ4 ኛ ክፍል እስከ ዩንቨርስቲ ያሉ አንድ ለአምስት በመደራጀት በህ.ወ.ሃ.ት ፈሽስታዊ ባህርያት እየታነፁ ፀረ ዲሞክራሲ ስራ በመፈፀም እንዲሰለፉ አየተደረገ ነው። በሕ/ሰቡ ውስጥ በሱስ የደነዘዙ፤ የተጠሉ ምንም ሰብአዊነት የሌላቸው ወጣቶችና ህፃናት የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች በገንዘብ እየደለሉ ህግ-መንግስትን አክብረዉ የሚታገሉ ፓርቲዎችንና ወገኖች በድንጋይ እንዲደበደቡ በማድረግ ደማቸዉ በጎዳና እየጎረፈ ይታያል ታስረዋል ካሜራቸውንና ሞባይላቸውን ተቀምተዋል። ለዚሁ እንደምሳሌ ለማሰቀመጥ በአዲግራት አፅቢ ወንበርታ በእንደርታ ወረዳ እድሜአቸዉ ከ3 እሰከ 12 አመት ህፃናት ለዓረና መድረክ አባላት ደብድበዋል የዜጎች /የታጋዮች ደም/ በአስፓልት ጎዳና/ፈሰዋል በተምቤን ዓበይ ዓዲ በሃገረሰላም በውቕሮ በሕሞራ በሽሬ በማይጨዉ በመቐለ በአላማጣ በዓድዋ ህዝብ የተቃዋሚዎች አማራጭ ሃሳብ እንዳይሰማ ወደ ስብሰባ እንዳይሄድ በፖሊሶች በደህንነት በቀበሌ ባንዳዎች በየቤቱ ጥበቃ ንዳይወጡ ተደርጓል። ያንሁሉ አፈና ጥሰዉ ወደ ስብሰባ የገቡ ዜጎች ከስብሰባ በኃላ ባለስልጣናት እየጠሩ ምክንያት እየፈጠሩ ማሰር ሌላዉ ቀርቶ የቀበሌ መታወቂያ መከልከል ዜግነታቸዉ መንጠቅ ይታያል። የፓርቲ ኣባላትም መታወቂያ እንዳይታደላቸዉ ተደርጓል ለምሳሌ መጥቀስ አያሌዉ በየነ ትውልድ ቀዬዉ አክሱም ውቕሮ ማራይ ወረዳ በውቕሮ ወረዳ በውቕሮ ከተማ ቀበሌ የሚኖር መታወቂያ አናድስልህም ተብሎ ለ4 አመት እየተሰቃየ ይገኛል። ለማረጋገጥ የሚፈልጉ ብዙሃን መገናኛ በ ስ.ቁ 0914 19 17 19 ጠይቁት።

በፋሽስታዊ ህወሃት አመራርና ባሁኑ ጊዜ ሲታይ ባሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲ እንቅስቃሴ በተለይ ደግሞ በመድረክ ኣባላት የሆኑ የዓረና ትግራይና የአንድነት ፓርቲ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚያደርጉት አማራጭ ሃሳባቸውን ወደ ገጠርና ከተሞች ዘልቀዉ ያደረጉት እንቅስቃሴ ለህ.ዋ.ሃ.ት ፋሽስታዊ መዋቅር / መርበብ/ በጣጥሰዉ ያሳለፉት መልእክት ሁሉም ህዝብ ስለተቀበላቸዉ በተለይ ደግሞ የህ.ዋ.ሃ.ት ፋሽስታዊ መሪዎች እንደመደበቂያ ዋሻ ሲጠቀሙበት የነበረዉ የትግራይ ህዝብ አሁን በህ.ዋ.ሃ.ት አመራር ፋሽስታዊ ተግባር ስለመረረዉ አልፎ አልፎም ለወረዳና ለቀበሌ አመራር ማመፅ ለከፍተኛ የክልሉና የህ.ዋ.ሃ.ት አመራር መሳደብ መናቅ ስለጀመረ እጅጉን ስላሳሰባቸዉ በጭንቀት ላይ ይገኛሉ። ይህን ጭንቅ ለመፍታት - ስዩም መስፍን የሚመራዉ ቡድን በቅርብ በብራስለስ እየታከሙ ነዉ ተብሎ ሲነገርለት የቆየዉ ስብሃት ነጋ አባይ ፀሃዬ ሃለቃ ፀጋይ በርሀ ከራያ እስከ ሽሬ ያሉ ከተሞችና የገጠር ነዋሪዎች በመንቀሳቀስ ስልጣን ጣፋጭ ነውና ወደ ህዝብ እየዞሩ በተለይ ደግሞ ዓረና ትግራይ
ሰፊ እንቅስቃሴ ያደረገባቸዉ ከተሞችና ገጠር ግለሰቦች በማግኘቴ ለመነጋገር እንኳን ቢፈልጉ የስድብ ናዳ እየወረደባቸዉ ስላለ
ሸሽተዉ ወደ መቐለ ተመልሰዉ እስከ አሁን አላማዉ ያልታወቀ ከመላዉ ትግራይ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞን አመራርና ልዩ ካድሬዎች ደህንነት በሚያደርጉት ዝግ ስብሰባ ( ኮንፍረንስ) በመሳተፍ ህዝብ ስለከዳን ለምርጫ 2007 ዓ/ም እንዴት አድርገን ድምፁን እንዲሰጠን እናድርግ በማለት በሃወልት ሰማእታት ፣ በፕላኔት ሆቴል በሚላኖ ሆቴል አዳራሾች በስብሰባ ላይ ተጠምደዉ ይገኛሉ።

- ሁሉንም ሰዉ ያስገረመዉ ግን በትግራይ ክልል በብዙ ሺ የሚቆጠር በሙስና የናጠጡ ካድሬ እያለ እነ ስዩምና ስብሃት ነጋ ኣባይ ፀሃዬ ፀጋይ በርሀ ሌሎችም ወደ ቀበሌ ወርደዉ ከህዝብ ጋር ለመታረቅ ጥረት ማድረግ ምን ያህል የህ.ዋ.ሃ.ት አመራር ከአባላቱ እንደተነጠሉና በመዋቅሩ እምነት እንዳጣ የሚያሳይ ነዉ።ይህ ደግሞ ፋሽስቶች ማንነታቸዉ በህዝብና በማዋቅራቸዉ ታውቀውና ተንቀዉ ውድቀታቸው ሲደርስ ተስፋ ቆርጠዉ ራሳቸዉ ወርደዉ እንደ ተራ ካድሬ ዲስኩር ያሰማሉ ይህ ተግባር ቀደም ሲል በሂትለርና በመሶለኒ ታይቷል። ትናንትም በመንግስቱ በጋዳፊ ወ.ዘ.ተ ታይቷል። የህ.ዋ.ሃ.ት ፋሽስታዊ አመራር የአጎቶቹ የነመንግስቱ እጣ አጋጥሞት ከዛ በላይ ካከዳዉ እየተጋጨ እነዚህ የ 70 እና የ80 አመት አዛውንት ፋሽስታዊ አገዛዛቸዉ እንዳይነጠቁ በዚህ በአብይ ፆም ሃይለኛ ፀሃይ ብቻቸውን እያበዱ ይግኛሉ።
- ከህዋሃት መንደር ምንጮች እንደሚያናፍሱት የህ.ዋ.ሃ.ት አመራር ከቁንጮ እስከ ቀበሌ ታማኝነታቸዉ ከህዝብ ስላጡ አሁን
የመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መልካም አስተዳደር ፍትህና ነፃነት ስላጣ ባለስልጣናት በሙስና ስለተበላሹ ታማኝነታቸውን ወደ ዜሮ
ስለወረደ በህዝብ ታማኝነት ልናገኝ ከተፈለገ ህዝቡን አሳማኝ የሆኑ ከሙሰኞች ከፀረ-ዲሞክራሲ ጫፎች እያለፍን እንምታ ብለዉ
ድምዳሜ ላይ እንደደረሱ ምንጮች ይናገራሉ በመሆኑመ በኣሁኑ ጊዜ የህ.ዋ.ሃ.ት ፋሽስታዊ መዋቀር በፍርሃት እየተናጠ ይግኛል።
- አሁን የሚያስቡት የማተለል ስልት በትግራይ ህዝብ በገበሬዉ በምሁሩ በባለሃብት በነጋዴዉ ምንም አይነት ተቀባይነት የለዉም 23 አመት ሙሉ እንደ እስስት እየተቀያየሩ እንደቀበሩት ስለተረዳ ነዉ
- ምናልባት አንዳንድ ወገኖች የህ.ዋ.ሃ.ት አመራር ፋሽስታዊ ባህርያት ዛሬ ነዉ የተከሰተዉ ትሉ ይሆናል በበኩሌ ህ.ዋ.ሃ.ት
ከተፈጠረበት ዘመን ጀምሮ ከህ.ዋ.ሃ.ት ፖለቲካ እምነቶች ውጭ ሌላ ሃሳብ የሚያራምዱ ሃሳቤን ያላመነ ጥይት ኣጉርሰዉ እያለ እንደመጣና
ብዙ ፓርቲዎች ግልሰቦች እየዋጠ እንደመጣ በተለያዩ ጊዜያት ግልፅ አድርጌ ነበር።
- ከ 1983 እና ከዛ በኃላ የነበሩት ጊዜያት ግን ምንም እንኳን እንደነ ሂትለርና መንግስቱ ነጋሪት ባይጎስም ጥሩምባ ባይነፋም በተግባር ግን ብዙ ፖለቲካ ፓርቲ እጅግ ብዙ ጋዜጠኞች በዙ ምሁራን እንዲጠፉ እንዲሰደዱ እንዲታሰሩ እንዲቀጡ አድርጓል። የሃገራችን ሃብትም በሙስና ተበልቷል ተመዝብሮ ውጭ አገር ሰፍሯል። የህ.ዋ.ሃ.ት አመራር በሃገራችን የሌለ ዲሞክራሲ አለ የሌለ ብልፅግና በልፅጓል ብሎ ዋሽቷል የህዝባችን ታሪክ አበላሽተዋል ሉአላዊነት ሃገር ተደፍረዋል መሬታችን የባህር በራችን አሳጥቷል 90 ሚሊዮን ህዝብ የመሬት ባለቤትነቱን አጥቶ ዜግነቱ ተነጥቀዋል ታዲያ የህ.ዋ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ደ.ግ አመራር ዘመናዊ ፋሽስት ከማለት ውጭ የተሻለ ስም ምን እንስጠዉ። ምክንያቱም ተደብቆ ቆይቶ ተደማምሮ ፋሽስታዊ ተፈጥሮዉ ሊደብቅ ቢፈልግ መደበቂያ ዋሻ አይገኝለትም። ይልቁንም የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ፋሽስታዊ ጎርፍ አፍሶ እንዳያጠፋን ሁሉም የኢትዮጵያ ህዘብ በመተባበር የጥንት ወላጆቹ ጠብቀውት በቆዩት ሃገር ሉአላዊነት አንድነት ፍቅርና መተሳሰብ ያስፍን የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎችና ስሪታቸዉ የሆኑ አባላት በታኝና ከፋፋይ ስርአት ከእንግዲህ ይቁም

ከሰላምታ ጋር

አስ ገደ ገ/ስላሴ፣ መቐለ

No comments:

Post a Comment